“ የግል ሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለልም መወሰን አለበት፤ እነዚህ ሠራተኞች መጀመሪያውኑ እየኖሩ አይደለም፤ 1500 የሚከፈለው ሠራተኛ ከወር በምንም ተዓምር ሊደርስ አይችልም ” - አቶ ካሳሁን ፎሎ
ከመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ባሻገር ለዘመናት ሲጠየቅ የቆየው የግል ሠራተኞች የደመወዝ ወለልም ተወስኖ በአስቸኳይ ምላሽ ካልተሰጠው በወር 1500 ብር የሚከፈላቸው ዜጎች አሁንም በቅጡ እየኖሩ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገረ።
ይህን ያሉት የግል ሠራተኞች የደመወዝ ወለል እስካሁን ያልተወሰነበት ምክንያት ምንድን ነው ? በሚል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ናቸው፡፡
ፕሬዚዳንቱ ለዚሁ ጥያቄ በሰጡን ማብራሪያም፣ “ የግል ሠራተኞችና የመንግስት ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ሕግና መዋቅር ይለያያል፣ ጥያቄው በተመሳሳይ የደመወዝ ጥያቄ ቢሆንም የሚመለስበት መንገድ ይለያያል፡፡ መንግስት የሚከፍላቸው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ሲቪል ሰርቫንትን የሚመለከት ነው ” ብለዋል።
የመንግስትና የግል ድርጅቶች በሚመለከት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እንደሚተዳደሩ፣ በዚሁ አዋጅ መነሻ የደመወዝ ወለል የሚወስን የገበያ ሁኔታ እያየ በየዓመቱ የሚያካክስ የደመወዝ ቦርድ ይቋቋማል እንደሚል ጠቅሰው፣ “ ያ የደመወዝ ቦርድ ተቋቁሞ ነው በጥናት የተመሰረተ ውሳኔ የሚሰጠው፡፡ ከመጀመሪያው ይሄ አዋጅ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ቦርድ እንዲቋቋም ስንጠይቅ ነበር፣ አሁንም እየጠየቅን ነው” ሲሉም አክለዋል።
“መንግስት የመንግስት ሠራተኛውን ደመወዝ በመጨመር ተነሳሽነቱን ወስዷል፤ እንደዚሁ ሁሉ የደመወዝ ቦርድም በአስቸኳይ ተቋቁሞ የግል ሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል መወሰን አለበት፤ ያለበለዚያ እነዚህ ሠራተኞች መጀመሪያውኑ እየኖሩ አይደለም፤ 1500 የሚከፈለው ሠራተኛ ከወር በምንም ተዓምር ሊደርስ አይችልም” ነው ያሉት።
“በትርፍ ላይ የተመሰረተ ሥራ የሚሰሩ ድርጅቶች ይህነንኑ መነሻ የደመወዝ ወለል እየጠበቁ ነው ያሉት” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ “ባለሃብቶችም ጋርም ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በሕጉ ላይ ሲቀመጥ መጀመሪያውኑ ውይይት ተደርጓል፣ እንዲያውም 'ለምን ዘገየ'? ብለው እየጠየቁ ነው፡፡ ይህን ደንብ የሚያወጣው ደግሞ መንግስት ነው” ብለዋል፡፡
አቶ ካሳሁን አክለው፣ “በ2018 ዓ/ም ይሄ ደንብ ወጥቶ መነሻ የደመወዝ ወለል፣ ይወሰናል፣ ሰራተኛው እኩል የሚደሰትበትን እድል ይፈጠራል ብለን እየጠበቅንና እየጠየቅን ነው፣ ረሃብ ጊዜ አይሰጥም” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
“ደንብ ማውጣት ነው፣ በደንቡ መሰረት ቦርዱ እንዲወስን ማድረግ ነው ሌላ የተለዬ ነገር የለውም፡፡ ይህን ለማድረግ ግን ሰባት ዓመታት ነው የቆየው፡፡ ይሄ በጣም ዘግይቷል፤ ከመንግስት ሠራተኞች ጥያቄ በፊትም ሲነሳ የነበረ ነው፡፡ የመንግስት ሴክተሩ ጥያቄ ተመልሷል፤ ሌሎቹም ዜጎች ናቸው፣ ዜጎቹ ደግሞ በአንድ በኩል እየተራቡ ነው” ብለዋል፡፡
“አሁን ሥራና ክህሎት የጀመረው ነገር አለ፣ እሱን በአስቸኳይ ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ደንቡ ወጥቶ በአስቸኳይ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ካልተወሰነ በስተቀር በተለይ የግል ተቋማት የሚሰሩት ሠራተኞች መኖር አይችሉም፤ አብዛኛው ዝቅተኛ የደመወዝ ተከፋይ ነው” በማለት አሳስበዋል፡፡
መንግስት ጨመርኩት ያለው የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ “ቀድሞውንም ከፍተኛ ተከፋይ ለሆኑት ሠራተኞች ያደላና ዝቅተኛ ተከፋዮችን ያላማከለ ነው” በሚል ስለሚነሳውን ቅሬታ ፌደሬሽኑ ምን ምላሽ እንዳለውም ፕሬዚዳንቱን ጥይቀናቸዋል፡፡
እሳቸውም፣ “ሁል ጊዜ የሆነ ሥራ ሲሰራ ወጥ ላይሆን ይችላል፡፡ አሁን ጭማሬው መደረጉ ጥሩ የሚለውን ነገር መውሰድ አለብን፡፡ ከዚህ በፊትም ከ1500 ወደ ወደ 4760 ሲገባ ላይ ያሉት ደግሞ 'መንግስት የታችኛውን ብቻ ነው ያየው፣ የላይኛውን አላየም' የሚል ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር፡፡ በላንሱን ማየት ያስፈልጋል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
“የመጀመሪያ ድግሪ ላይ ትንሽ ጨምሯል በእርግጥ 11,500 ነው የሆነው፤ ይሄ ደግሞ ማለት ከበፊት ጋር ተያይዞ ሊሆን ስለሚችል ላገኘው እንኳን አገኘ፣ ለሌላው ደግሞ ይሁን እየበላን ጥያቄያችንን መቀጠል አለብን እንጅ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማስደሰት አይቻልም” ብለዋል፡፡
“ጭማሪው በቂ አይደለም” በሚል እየተነሳ ያለውን ጥያቄ በተመለከተም፣ “በደመወዝ ጭማሪ ብቻ ኑሮ ውድነቱን መቋቋም ስለማይቻል 10 ሺሕ ቢደረግ ይበቃል ማለት አይደለም፡፡ ግን መንግስት ከመክፈል አቅሙ አንጻር አይቶ ይህን ምላሽ በመስጠቱ ነው ጥሩ የምንለው፡፡ መንግስትም 'ሌሎች ጥቅማጥቅሞች በሰራተኞች የሚታሰቡበት ሁኔታ አለ' ብሏል፤ ምክንያቱም በደመወዝ በመጨመር ብቻ የኑሮ ውድነቱን ማቆም አይቻልም” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አሁን ከተደረገው የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ባሻገር ምን መደረግ እንዳለበት ሲጠየቁም፣ “ሕገወጥ ድርጊት በሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ መወሰድ አለበት፣ ሁሉም ነጋዴ ሕገወጥ ነው ማለት አይደለም፤ ግን የሆነ ነገር ሲከሰት በአጭር መንገድ መክበር የሚፈልጉ አሉ” የሚል ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Play Store