#ታርጋ
በኢትዮጵያ የሚመዘገቡ ሁሉም ተሽከርካሪዎች 'ኢት' የሚል መለያ እና የኢትዮጵያ ካርታ ያለበት አዲስ የመለያ ሠሌዳ ቁጥር እንዲኖራቸው ሊደረግ ነው።
በአገሪቱ ያሉ ተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሠሌዳ እንደሚቀየር ተነግሯል።
በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የወጣው መመሪያ ምን ይዟል ?
- አዲሱ መመሪያ በአሁኑ ሰዓት በሥራ ላይ ያሉ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች ላይ የሚቀመጠውን የተለያዩ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መለያዎችን አላካተተም።
- በመላው ኢትዮጵያ አገልግሎት ላይ የሚውሉት የሠሌዳ ቁጥሮች ተመሳሳይ መለያ እንዲኖራቸው ይደረጋል።
- ሁሉም የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሠሌዳዎች በእንግሊዝኛ እና በግዕዝ ፊደላት ኢትዮጵያን የሚያመለክት አጭር ጽሁፍ እና የኢትዮጵያ ካርታ ይኖራቸዋል።
- በሀገሪቱ የሚመዘገቡ ሁሉም ተሸከርካሪዎች የሚለጥፉት የመለያ ቁጥር ሠሌዳ ላይ የኢትዮጵያ ካርታ እና ኢትዮጵያ ባጸደቀችው ዓለም አቀፍ ስምምነት መሠረት የተሰጣትን ሀገራዊ ልዩ ምልክት "ETH" እንዲሁም "ኢት" የሚል የግእዝ ፊደላት እና የላቲን ፊደላት ይዘት እንዲኖረው ይደረጋል፡፡
- የመለያ ቁጥር ሠሌዳ አሰጣጡ ሦስት የላቲን ፊደላትን እና አራት ቁጥሮችን በመጠቀም ተከታታይ ቁጥር ያላቸው የመለያ ቁጥር ሠሌዳዎችን እንዲመረቱ ይደረጋል።
- የተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሠሌዳዎች የቀለም ኅብር፣ ፊደላት በተጨማሪ የመለያ ቁጥር ሠሌዳዎቹ ሲመረት ለቁጥጥር እና ለምዝገባ ዓላማ የሚያገለግሉ መረጃዎችን የሚሰጡ ምሥጢራዊ ምልክቶችን እያንዳንዱ የሠሌዳ ዓይነት እንዲኖረው ይደረጋል።
- የመለያ ቁጥር ሠሌዳዎቹ የተሽከርካሪዎችን ባለቤት፣ የሚሠጡትን አገልግሎት እና የኃይል አጠቃቀምን የሚያመለክቱ ቀለማት እንዲሁም ሌሎች መለያዎች ይኖራቸዋል።
- በኤሌክትሪክ ወይም ታዳሽ ኃይሎች የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ከሌሎች በተለየ መልኩ " አረንጓዴ ትራንስፖርት (Green Transport) " የሚል የጽሁፍ መለያ ይይዛል።
- ልዩ መግለጫ ያለው የተለየ የመለያ ቁጥር ሠሌዳ የሚፈልጉ ግለሰቦች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ለሚጠይቅ እንደሁኔታው በልዩ ሁኔታ ሊሰጣቸው ይችላል።
- አዲሱ የሠሌዳ ዓይነት ከዚህ ቀደም በተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች ላይም ተግባራዊ ይሆናል።
- መመሪያው በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች የቀድሞውን ሠሌዳ ለመዝጋቢው አካል በመመለስ አዲስ የተሸከርካሪ የመለያ ቁጥር ሠሌዳ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- የተሽከርካሪ ባለቤቶች ነባሩን ሠሌዳ በመመለስ አዲሱን የሚወስዱት የትራንስፖር እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ነው።
በአጼ ሚኒሊክ ዘመን የመጀመሪያዋ ተሽከርካሪ ወደ ኢትዮጵያ ከገባች ጊዜ አንስቶ ለመኪኖች የመለያ ቁጥር መሠጠት እንደተጀመረ የሚነገር ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ወደ ሥልጣን በመጡት አስተዳደሮች ቢያንስ ሦስት ጊዜ የተሽከርካሪዎች መለያ ሠሌዳ ቁጥር ለውጥ ተደርጓል።
በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበረው የሠሌዳ ቁጥር፣ ወታደራዊው መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ የተቀየረ ሲሆን፣ በደርግ ዘመን የነበረው ደግሞ ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ለውጥ ተደርጎበታል።
በኢህአዴግ ዘመን ለአገልግሎት የበቃው እና እስካሁንም በሥራ ላይ ያለው የተሽከርካሪዎች መለያ ቁጥር ሠሌዳ 'ኢት' የሚል መለያ ካላቸው ከተወሰኑ ተሽከርካሪዎች ውጪ አብዛኞቹ የሚንቀሳቀሱባቸውን ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ስም ሁለት ፊደላትን የያዙ ናቸው።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

Play Store